ኢትዮጵያ ሴቶች ትንሳኤ

ዕፁብ ድንቅ ኢትዮጵያውያን ሴቶች

Ethiopian Women Unleashed

Phenomenal Ethiopian Women

የኢትዮጵያ ሴቶች ትንሳኤ (እመርታ)

ወደ “ኢትዮጵያ ሴቶች ትንሳኤ” እንኳን በደህና መጡ።

የእነዚህ ስኬታማ ሴቶች ህይወት፣ ለኢትዮጵያ ወጣት ሴቶችና ልጃገረዶች (ለሌላውም አለም ጭምር)፣ መንፈስን የሚያነቃቃ አርአያ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን። ባለታሪኮቹ ሴቶች፤ በአጥር የተከለለውን ልማዳዊ የህይወት አለም አሜን ብለው ሳይቀበሉ ድንበሩን በመግፋትና በመገርሰስ፣ በተለያየ መንገድ ለራሳቸውና ለሌሎች፣ አዳዲስ የህይወት አማራጮችን የቀየሱ የጀግንነት ተምሳሌት ናቸው። የተወለዱበትና ያደጉበት አውድ፣ እንዲሁም የመጡበት የህይወት መንገድ… የተለያየ ነው። ከገጠር እስከ ከተማ፣ ከአገር ቤት እስከ ዳያስፖራ አመጣጣቸው ለየቅል ቢሆንም፣ ለኢትዮጵያ ሴቶች በርካታ የስኬት አማራጮችን በመፍጠር ውጤታማ ለውጥ ያስመዘገቡ ሴቶች ናቸው – በቤተሰብም ሆነ በማህበረሰብ፣ በአገርም ሆነ በአለም ደረጃ። ጥቂቶቹ  በቀድሞው የአገራችን ታሪክ የሚታወቁ ሲሆኑ፤ አብዛኞቹ ደግሞ የዘመናችን ሴቶች ናቸው። ነገር ግን ሁሉንም የሚያመሳስላቸው የጋራ መለያ አላቸው። ጠንካራና ብርቱ፣ ደፋርና ቁርጠኛ፣ እንዲሁም ብዙዎቹ ለወገኖቻቸው አንዳች ፋይዳ ለማበርከት እጅጉን የተጉ ሴቶች ናቸው። የእኒህ ጀግኖች ታሪክ፣ የእስከዛሬውን ስኬት ከማሳየት አልፎ፣ ወደፊትም ኢትዮጵያና መላው አለም ገና ብዙ አጃኢብ የሚያሰኝ ተአምር እንደሚጠብቃቸው የሚጠቁም ነው። እንዴት ቢሉ፣ እያንዳንዷ የኢትዮጵያ ወጣት ሴት ምቹ ሁኔታ አግኝታ እምቅ አቅሟን በሙሉ አውጥታ የተነሳች ጊዜ፣ እልፍ የስኬት (የእመርታ) ታሪክ ይፈጠራል።

Temsalet book coverpng

ሆኖም ተጀመረ እንጂ አላለቀም። መች ተነካና! ገና ብዙ ያልተሰበሰበ የኢትዮጵያ ስኬታማ ሴቶች ታሪክ አለ። እስካሁን ያሰባሰብናቸው ታሪኮች፣ መነሻ ይሆናሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ከዘመናችን ስኬታማ ሴቶች መካከል፣ ባለፉት ሦስት ዓመታት  ያወቅናቸውንና አፈላልገን ያገኘናቸውን የተወሰኑ ሴቶች ቃለምልልስ በማድረግ ታሪካቸውን አቅርበናል። ከቀድሞው ዘመን ስኬታማ ሴቶች መካከልም፣ በነበረን ውስን የጥናት ጊዜ ውስጥ ያሰባሰብናቸውን ታሪኮች ብቻ አካተናል፡፡ የዘመናችን ሴቶች ታሪክ ውስጥ የተጠቀሱት መረጃዎች በሙሉ፤ ከባለታሪኮቹ ጋር በተደረገ ቃለምልልስ የተገኙ ሲሆኑ ቃለምልልሱ የተቀረፀው፣ወጣት ሴቶች ቀጣይ ህይወታቸውን ለመምራት የሚያስችል ጠቃሚ ተሞክሮ ከባለታሪኮቹ እንዲያገኙ ታሳቢ በማድረግ ነው። በስኬታማነታቸው የሚታወቁና ታሪካቸው እንዲካተት ያሰብናቸው በርካታ ሴቶች ነበሩ። ሆኖም፣ በጥናት ጊዜያችን፣ ፈልገን ስላላገኘናቸው ሳይካተቱ ቀርተዋል። ገና ያላወቅናቸው ብዙ ስኬታማ ሴቶች እንዳሉም እንገነዘባለን። ወደፊት ታሪካቸውን እያሰባሰብን ማቅረባችንን እንገፋበታለን።

ውድ አንባቢያን፤ እናንተም መካተት አለባቸው የምትሏቸውን ስኬታማ ሴቶች በመጠቆም የበኩላችሁን እንድታበረክቱ በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ለዚህም “እርስዎም ይሳተፉ” የተሰኘውን ድረገፃችን በመጠቀም፣ የስኬታማ ሴቶች ስምና አድራሻ፣ እንዲሁም ስለሴቶቹ የሚገልፅ  ጥቂት መረጃ በኢሜይል ይላኩልን። ድንቅ ድንቅ ስኬታማ ሴቶችን እያፈላለገ ቃለምልልስ ለማካሄድና ታሪካቸውን ለማሰባሰብ የተዘጋጁ አጥኚዎች የናንተን መረጃ በጉጉት ይጠብቃሉ። አስደማሚ ስኬት ያስመዘገቡ ሴቶችን ቃለምልልስ በማድረግ ልታግዙን የምትፈልጉ በጎ ፈቃደኞች፣ ግብዣችን ይድረሳችሁ። የበጎ ፍቃድ ተሳታፊዎች፤ በትዕግስትና በጥሞና የማዳመጥ፣ እንዲሁም በእንግሊዝኛና በአማርኛ አሳምሮ የመፃፍ ችሎታ ይጠበቅባቸዋል።

ያንብቡ፣ ይደሰቱ

  • All Posts
  • EWU Women
ሂሩት ወልደማርያም

ስኬታማ ሴቶች ህይወት ሂሩት ወልደማርያም ዋና ዋና ስኬቶች: በሥነ ልሳን ፈጣን የተባባሪ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያገኘች፣ የመጀመርያዋ ሴት የአካዳሚ ጉዳዮች ተባባሪ…

መዓዛ ከበደ መካ

ስኬታማ ሴቶች ህይወት መዓዛ ከበደ መካ ዋና ዋና ስኬቶች: በተለይ ለሴቶችና ለህፃናት የውሃ እና የአካባቢ ንፅህና አገልግሎትን የማሻሻል ጥልቅ ልባዊ…

መክሊት አየለ ሀዴሮ

ስኬታማ ሴቶች ህይወት መክሊት አየለ ሀዴሮ ዋና ዋና ስኬቶች: የቴድ ግሎባል “ፌሎው” ሆና ተመርጣለች፤ ከትውልድ አገራቸው ጋር ትስስራቸውን ለማጎልበት በቁርጠኝነት የሚታትሩ የዳያስፖራ…

ሃና ተሾመ ወልደፃዲቅ

ስኬታማ ሴቶች ህይወት ሃና ተሾመ ወልደፃዲቅ ዋና ዋና ስኬቶች: የሃና ወላጅ አልባ ህፃናት ማሳደጊያ መስራችና ዳይሬክተር ናት፡፡ በ26 ለቤተሰብ በሚሆኑ…

ሶፊያ በቀለ እሸቴ

ስኬታማ ሴቶች ህይወት ሶፊያ በቀለ እሸቴ ዋና ዋና ስኬቶች: በሲስተምስ ኢንተግሬሽን ሥራዎች ላይ ያተኮረ ሲቢኤስ ኢንተርናሽናል የተሰኘ ኩባንያ በአሜሪካያቋቋመች ሲሆን፣…

ሳባ ኪዳነማርያም ገብሩ

ስኬታማ ሴቶች ህይወት ሳባ ኪዳነማርያም ገብሩ ዋና ዋና ስኬቶች: IPAS የተባለው ድርጅት የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ወቅታዊ ሁኔታ: አክሱም፣ ትግራይ፣ ኢትዮጵያ የትውልድ…

Roman Deksiso

ስኬታማ ሴቶች ህይወት ሮማን ዴቅሲሶ በዳሶ ዋና ዋና ስኬቶች: የባለቤቷን መታሰር ተከትሎ፣ በአዳማ የተከበረና ስኬታማ የእህል ንግድ መስርታለች፤ የአዳማ ሴት…

Load More

End of Content.

ዕፁብ ድንቅ ኢትዮጵያውያን ሴቶች

ተምሳሌት መፅሐፍ

2023 © Network of Ethiopian Women’s Association