ስኬታማ ሴቶች ህይወት ደስታ ገብሩ ደስታ ዋና ዋና ስኬቶች: የጦር ሠራዊት ሚስቶች ማህበር መስራችና ፕሬዚዳንት በመሆን ወላጆቻቸውን ላጡ የወታደር ልጆች…
የእነዚህ ስኬታማ ሴቶች ህይወት፣ ለኢትዮጵያ ወጣት ሴቶችና ልጃገረዶች (ለሌላውም አለም ጭምር)፣ መንፈስን የሚያነቃቃ አርአያ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን። ባለታሪኮቹ ሴቶች፤ በአጥር የተከለለውን ልማዳዊ የህይወት አለም አሜን ብለው ሳይቀበሉ ድንበሩን በመግፋትና በመገርሰስ፣ በተለያየ መንገድ ለራሳቸውና ለሌሎች፣ አዳዲስ የህይወት አማራጮችን የቀየሱ የጀግንነት ተምሳሌት ናቸው። የተወለዱበትና ያደጉበት አውድ፣ እንዲሁም የመጡበት የህይወት መንገድ… የተለያየ ነው። ከገጠር እስከ ከተማ፣ ከአገር ቤት እስከ ዳያስፖራ አመጣጣቸው ለየቅል ቢሆንም፣ ለኢትዮጵያ ሴቶች በርካታ የስኬት አማራጮችን በመፍጠር ውጤታማ ለውጥ ያስመዘገቡ ሴቶች ናቸው – በቤተሰብም ሆነ በማህበረሰብ፣ በአገርም ሆነ በአለም ደረጃ። ጥቂቶቹ በቀድሞው የአገራችን ታሪክ የሚታወቁ ሲሆኑ፤ አብዛኞቹ ደግሞ የዘመናችን ሴቶች ናቸው። ነገር ግን ሁሉንም የሚያመሳስላቸው የጋራ መለያ አላቸው። ጠንካራና ብርቱ፣ ደፋርና ቁርጠኛ፣ እንዲሁም ብዙዎቹ ለወገኖቻቸው አንዳች ፋይዳ ለማበርከት እጅጉን የተጉ ሴቶች ናቸው። የእኒህ ጀግኖች ታሪክ፣ የእስከዛሬውን ስኬት ከማሳየት አልፎ፣ ወደፊትም ኢትዮጵያና መላው አለም ገና ብዙ አጃኢብ የሚያሰኝ ተአምር እንደሚጠብቃቸው የሚጠቁም ነው። እንዴት ቢሉ፣ እያንዳንዷ የኢትዮጵያ ወጣት ሴት ምቹ ሁኔታ አግኝታ እምቅ አቅሟን በሙሉ አውጥታ የተነሳች ጊዜ፣ እልፍ የስኬት (የእመርታ) ታሪክ ይፈጠራል።
ሆኖም ተጀመረ እንጂ አላለቀም። መች ተነካና! ገና ብዙ ያልተሰበሰበ የኢትዮጵያ ስኬታማ ሴቶች ታሪክ አለ። እስካሁን ያሰባሰብናቸው ታሪኮች፣ መነሻ ይሆናሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ከዘመናችን ስኬታማ ሴቶች መካከል፣ ባለፉት ሦስት ዓመታት ያወቅናቸውንና አፈላልገን ያገኘናቸውን የተወሰኑ ሴቶች ቃለምልልስ በማድረግ ታሪካቸውን አቅርበናል። ከቀድሞው ዘመን ስኬታማ ሴቶች መካከልም፣ በነበረን ውስን የጥናት ጊዜ ውስጥ ያሰባሰብናቸውን ታሪኮች ብቻ አካተናል፡፡ የዘመናችን ሴቶች ታሪክ ውስጥ የተጠቀሱት መረጃዎች በሙሉ፤ ከባለታሪኮቹ ጋር በተደረገ ቃለምልልስ የተገኙ ሲሆኑ ቃለምልልሱ የተቀረፀው፣ወጣት ሴቶች ቀጣይ ህይወታቸውን ለመምራት የሚያስችል ጠቃሚ ተሞክሮ ከባለታሪኮቹ እንዲያገኙ ታሳቢ በማድረግ ነው። በስኬታማነታቸው የሚታወቁና ታሪካቸው እንዲካተት ያሰብናቸው በርካታ ሴቶች ነበሩ። ሆኖም፣ በጥናት ጊዜያችን፣ ፈልገን ስላላገኘናቸው ሳይካተቱ ቀርተዋል። ገና ያላወቅናቸው ብዙ ስኬታማ ሴቶች እንዳሉም እንገነዘባለን። ወደፊት ታሪካቸውን እያሰባሰብን ማቅረባችንን እንገፋበታለን።
ውድ አንባቢያን፤ እናንተም መካተት አለባቸው የምትሏቸውን ስኬታማ ሴቶች በመጠቆም የበኩላችሁን እንድታበረክቱ በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ለዚህም “እርስዎም ይሳተፉ” የተሰኘውን ድረገፃችን በመጠቀም፣ የስኬታማ ሴቶች ስምና አድራሻ፣ እንዲሁም ስለሴቶቹ የሚገልፅ ጥቂት መረጃ በኢሜይል ይላኩልን። ድንቅ ድንቅ ስኬታማ ሴቶችን እያፈላለገ ቃለምልልስ ለማካሄድና ታሪካቸውን ለማሰባሰብ የተዘጋጁ አጥኚዎች የናንተን መረጃ በጉጉት ይጠብቃሉ። አስደማሚ ስኬት ያስመዘገቡ ሴቶችን ቃለምልልስ በማድረግ ልታግዙን የምትፈልጉ በጎ ፈቃደኞች፣ ግብዣችን ይድረሳችሁ። የበጎ ፍቃድ ተሳታፊዎች፤ በትዕግስትና በጥሞና የማዳመጥ፣ እንዲሁም በእንግሊዝኛና በአማርኛ አሳምሮ የመፃፍ ችሎታ ይጠበቅባቸዋል።
ያንብቡ፣ ይደሰቱ
ስኬታማ ሴቶች ህይወት ደስታ ገብሩ ደስታ ዋና ዋና ስኬቶች: የጦር ሠራዊት ሚስቶች ማህበር መስራችና ፕሬዚዳንት በመሆን ወላጆቻቸውን ላጡ የወታደር ልጆች…
ስኬታማ ሴቶች ህይወት ብሩታዊት ጥጋቡ ታደሰ ዋና ዋና ስኬቶች: በኢትዮáያ ታሪክ የመጀመርያዋ ሴት የባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤ በአቢሲኒያ ባንክ ፣…
ስኬታማ ሴቶች ህይወት ብሩክታዊት ጥጋቡ ታደሰ ዋና ዋና ስኬቶች: ከሰባት አመት በታች ለሆኑ ሕፃናት ጠቃሚ መልዕክቶችን የሚያስተላልፍ “ፀሐይ መማር ትወዳለች”…
ስኬታማ ሴቶች ህይወት ሙሉመቤት ገብረሥላሴ ዋና ዋና ስኬቶች: በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ዘመናዊ የውበት ሳሎን እና የስፓ አገልግሎት ከፍታለች፤ የባዮጀኒክቢዩቲ ስፖት መስራችና…
ስኬታማ ሴቶች ህይወት ሀረገወይን ቸርነት ወልደማርያም ዋና ዋና ስኬቶች: የሴቶች ልማት የምርምርና ሥልጠና ማዕከል (CERTIUDE) (አሁን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስርዓተ…
ስኬታማ ሴቶች ህይወት ሂሩት በፈቃዱ ወልደሚካኤል ዋና ዋና ስኬቶች: የተባበሩት መንግስታት የሴቶች ጉዳይ ኮንፈረንስ በቤጂንግ በሚካሄድበት ወቅት፣ በአፍሪካ አንድነት ድርጅት…