“የኢትዮጵያ ሴቶች ትንሳኤ”፣ እጩ እንዲጠቁሙ ይጋብዝዎታል
መካተት አለባት ብለው የሚያስቧት ኢትዮጵያዊ ስኬታማ ሴት የሚያውቁ ከሆነ፤ ስሟንና አድራሻዋን፣ እንዲሁም ለምን በእጩነት እንደመረጧት የሚጠቁም ጥቂት መረጃ በኢሜይል ይላኩልን። በእጩነት የመረጧት ሴት፣ ቀድሞ በታሪክ የነበረች ወይም የአሁን ዘመን ልትሆን ትችላለች። የአድራሻ ገፅ የሚለውንም በመጠቀም መልእክታችሁን ልታደርሱን ትችላላችሁ።
እጩ ለመምረጥ ስታስቡ፣ ግምት ውስጥ ልታስገቧቸው የሚገቡ ነጥቦች፡
*የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነች (በኢትዮጵያ የምትኖርም ሆነ ዳያስፖራ)፤ ወይም የውጭ ዜጋ ብትሆንም ኢትዮጵያ ውስጥ ጉልህ ስራ ያከናወነች፤
* በተሰማራችበት የሥራ መስክ ስኬት የተቀዳጀች፣ ህብረተሰቡ ስለ ሴቶች ካለው የዘልማድ አመለካከት ጋር ታግላ፣ ለሴቶች ታጥሮ ከተከለለው ልማዳዊ ሚና ባሻገር ተጉዛ ህልሟን እውን ያደረገች፤
*አንድም የሴቶችን ግስጋሴ የሚገድቡ መሰናክሎችን ሰባብራ፣ አልያም በራሷ ህይወትም ሆነ በማህበረሰብ ውስጥ ያሉ እንቅፋቶችን በመጋፈጥ አሸንፋ፣ ወይም በተሰማራችበት እመርታ አስመዝግባ ስኬትን የተቀዳጀት፤
*ዝነኛ ብትሆንም ባትሆንም፣ በስኬቷ ገና በሰፊው ብትታወቅም ባትታወቅም፤ በአካባቢዋ ወይም በኢትዮጵያ አሊያም በዓለም ደረጃ ትርጉም ያለው ለውጥ ለመፍጠር የቻለች፤
በፈተናዎች የማይበገር ቁርጠኝነትንና ድፍረትን፣ አልሸነፍ ባይነትንና ፅናትን በማሳየት፤ የወጣት ሴቶችን መንፈስ ለማነቃቃት የሚችሉ የሕይወት ታሪኮች፣ ይበልጥ ተፈላጊ ናቸው። በተጨማሪም፣ ሌሎች ሰዎችን ለመርዳት ትጋት የሚያሳዩ ሴቶችም ታሪካቸው በጣም ይፈለጋል። የሚመርጧት እጩ በማንኛውም የእድሜ ክልል ላይ የምትገኝ፤ በህይወት ያለች ወይም በህይወት የሌለች ልትሆን ትችላለች።
መረጃዎቻችንን ለማሻሻል ያግዙን !
በዚህ ድረገፅ የቀረቡ ባለታሪክ ሴቶችን በሚመለከት፣ ታሪኩን የሚያበለፅግ ተጨማሪ መረጃ የሚያውቁ ከሆነ፣ ወይም የተዛባ ታሪክ ለማረም የሚረዳ መረጃ ካለዎት፤ እባክዎ የአድራሻ ገፅ የሚለውን በመጠቀም በኢሜይል ይላኩልን። ይሄም በማድረግ ታሪኮቹ ይበልጥ ትክክለኛና ጠቃሚ እንዲሆኑ ያግዙን።
ለተሳትፎዎ እጅግ በጣም እናመሰግናለን
"Alteration literature to or an sympathize mr imprudence. Of is ferrars subject as enjoyed or tedious cottage. Procuring as in resembled by in agreeable. Next long no gave mr eyes. Admiration advantages no he celebrated so pianoforte unreserved. Not its herself forming charmed amiable."
"The him father parish looked has sooner. Attachment frequently gay terminated son. You greater nay use prudent placing. Passage to so distant behaved natural between do talking. Friends off her windows painful. Still gay event you being think nay for. In three if aware he point it. Effects warrant feeling settled."
"Up is opinion message manners correct hearing husband my. Disposing commanded dashwoods cordially depending at at. Its strangers who you certainty earnestly resources suffering she. Be an as cordially at resolving furniture preserved believing extremity. Easy mr pain felt in. Too northward affection additions nay."