ስኬታማ ሴቶች ህይወት ደስታ ገብሩ ደስታ ዋና ዋና ስኬቶች: የጦር ሠራዊት ሚስቶች ማህበር መስራችና ፕሬዚዳንት በመሆን ወላጆቻቸውን ላጡ የወታደር ልጆች የማሳደጊያ ማዕከል አቋቁማለች። የሟች ወታደር ቤተሰቦች ማህበራዊ ደህንነት እንዲረጋገጥ አገራዊ ዘመቻ ከመምራቷም በተጨማሪ፤ የወታደር ሚስቶች ከቤት ውጭ ለሥራ እንዲሰማሩ በማበረታታትና ወጣት ሴቶችን በማሰልጠን ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክታለች። ፀሐይ ጮራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን በማቋቋም በርዕሰ መምህርነት […]
የምወድሽ በቀለ
ስኬታማ ሴቶች ህይወት የምወድሽ በቀለ ዋና ዋና ስኬቶች: የራሷን የአጭር ልብወለዶች መድበል በማሳተም የመጀመርያይቱ ኢትዮጵያዊት ሴት ናት፣ የመጀመርያዋ ሴት የፖሊስ ፕሬስ ክፍል ሃላፊ ሆና አገልግላለች፣ የኢትዮጵያ ሴቶች ደራስያን ማህበር ፕሬዚዳንት ናት፣ ከሰባት በላይ መፃህፍት የፃፈችና ያሳተመች ናት። ወቅታዊ ሁኔታ የኢትዮጵያ ሴቶች ደራስያን ማህበር ፕሬዚዳንት የትውልድ ቦታ: አዲስ አበባ የትውልድ ዘመን: ነሀሴ 1952 ዓ.ም ወቅታዊ መኖሪያ ስፍራ አዲስ አበባ […]
ብርሃኔ ዳባ
ስኬታማ ሴቶች ህይወት ብርሃኔ ዳባ ዋና ዋና ስኬቶች: ከአካል ጉዳተኝነት ጋር የተያያዙ ልማዳዊ ፍረጃዎችን ተጋፍጣ በማሸነፍ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ ለመሆን በቅታለች ፤አካል ጉዳተኞች የገቢ ማስገኛ ክህሎት ስልጠናና ከሌሎች እኩል ስራ የመቀጠር እድል እንዲያገኙ ልዩ ትኩረቱ አድርጎ የሚሰራውን የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኛ ሴቶች ማህበር ከሌሎች ጋር በመመስረት፣ በፕሬዚዳንትነት ትመራለች ወቅታዊ ሁኔታ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ፣ ብሄራዊ ቤተመፃህፍት ኤጀንሲ፣ […]
ብሩታዊት ዳዊት አብዲ
ስኬታማ ሴቶች ህይወት ብሩታዊት ጥጋቡ ታደሰ ዋና ዋና ስኬቶች: በኢትዮáያ ታሪክ የመጀመርያዋ ሴት የባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤ በአቢሲኒያ ባንክ ፣ በወጋገንና በኋላም በዘመን ባንክ መሥራች ዋና ሥራ አስፈፃሚ በመሆን ሰርታለች፤ በኢትዮáያ በርካታ አዳዲስና ዘመናዊ የባንክ አሰራሮችንና አገልግሎቶችን አስተዋውቃለች፤ የዘመኑን ምርጥና ቁንጮ የባንክ መሪዎችን በማሰልጠን አፍርታለች። ወቅታዊ ሁኔታ አዳዲስ አማራጮችን በማጥናትና በመመርመር ላይ ትገኛለች የትውልድ ቦታ: […]
ብሩክታዊት ጥጋቡ ታደሰ
ስኬታማ ሴቶች ህይወት ብሩክታዊት ጥጋቡ ታደሰ ዋና ዋና ስኬቶች: ከሰባት አመት በታች ለሆኑ ሕፃናት ጠቃሚ መልዕክቶችን የሚያስተላልፍ “ፀሐይ መማር ትወዳለች” የተሰኘየቴሌቪዥን ፕሮግራም በመፍጠር ተሸላሚ ሆናለች። አራተኛ አመቱን የያዘው የቴሌቪዥን ፕሮግራም በ5 ሚሊዮንሕፃናት ታይቷል። እድሜያቸው ከ10 እስከ 15 ዓመት የሆኑ ልጆች የሚሳተፉበትና ስለራሳቸው ሕይወት የአንድደቂቃ ቪዲዮ የሚያዘጋጁበት ፕሮግራምም ጀምራለች – “ኢንቮልቭ ሚ” በሚል ሥያሜ። ከ13 አመትና […]
ሙሉመቤት ገብረሥላሴ
ስኬታማ ሴቶች ህይወት ሙሉመቤት ገብረሥላሴ ዋና ዋና ስኬቶች: በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ዘመናዊ የውበት ሳሎን እና የስፓ አገልግሎት ከፍታለች፤ የባዮጀኒክቢዩቲ ስፖት መስራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ናት። የውበት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት አቋቁማ ከ680በላይ ሙያተኞችን አስመርቃለች። ከጓደኞቿ ጋር “ሳራ ካኒዛሮ ቻይልድ ማይንደር” የተሰኘ ማኅበርበማቋቋም ችግረኛ ልጆችን የሚረዳ መዋዕለ ሕፃናት ከፍታለች። ወቅታዊ ሁኔታ የባዮጀኒክ ቢዩቲ ስፖት ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ የትውልድ ቦታ: ወንጂ፣ ኦሮሚያ፣ ኢትዮጵያ የትውልድ […]
ሀረገወይን ቸርነት ወልደማርያም
ስኬታማ ሴቶች ህይወት ሀረገወይን ቸርነት ወልደማርያም ዋና ዋና ስኬቶች: የሴቶች ልማት የምርምርና ሥልጠና ማዕከል (CERTIUDE) (አሁን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስርዓተ – ፆታ ጥናቶች ተቋም) ቀደምት ዳሬክተሮች ከነበሩት አንዷ ናት፡፡ የሴቶችን ጥቃት ለማስቆም የምትሟገት፣ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች የሃይማኖት መሰረት አላቸው የሚለውን የተሳሳተ አመለካከት ለማጥፋት የሃይማኖት መሪዎችን በማስተባበር የፈርቀዳጅነቱን ሚና የተጫወተች፤ ለፈሪ ተለማማጅ መምህራን ድፍረትን የሚያስተምር “Assertiveness […]
ማጂ-ዳ አብዲ
ስኬታማ ሴቶች ህይወት ማጂ-ዳ አብዲ ዋና ዋና ስኬቶች: ሽልማት ያሸነፈ “The River that Divides” የተሰኘ ዶክመንታሪ ፊልም በፀሃፊነት፣ በፕሮዱዩሰርነትና በዳይሬክተርነት ሰርታለች፡፡ ፊልሙ በኢትየ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ከመኖርያቸው ተገደው ስለተፈናቀሉ ሴቶችና ህፃናት ታሪክ የሚናገር ነው፡፡ ስኬታማ የፊልም ፕሮዱሰር ናት፡፡ በ2002 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተዘጋጀ “Images That Matter” የተሰኘ የፊልም ፌስቲቫል አዘጋጅ ስትሆን በፌስቲቫሉ ላይ ለወጣት የምስራቅ አፍሪካ ፊልም ሰሪዎች ስልጠና […]
ሂሩት በፈቃዱ ወልደሚካኤል
ስኬታማ ሴቶች ህይወት ሂሩት በፈቃዱ ወልደሚካኤል ዋና ዋና ስኬቶች: የተባበሩት መንግስታት የሴቶች ጉዳይ ኮንፈረንስ በቤጂንግ በሚካሄድበት ወቅት፣ በአፍሪካ አንድነት ድርጅት (አአድ) ውስጥ የሴቶች ክፍል አቋቁማለች። የአፍሪካ የተግባር አቋም (African Platform for Action) የተሰኘውን ሰነድ ለማዘጋጀትና በቤጂንግ ጉባኤ 10ሺ የሚጠጉ የአፍሪካ ሴት ልዑካን ለማሳተፍ አስተባብራለች። አአድ በመላ አፍሪካና በተቀረው አለም ተአማኒነትን እንዲያገኝ ለ17 አመታት የመረጃ አገልግሎት […]
ሂሩት ወልደማርያም
ስኬታማ ሴቶች ህይወት ሂሩት ወልደማርያም ዋና ዋና ስኬቶች: በሥነ ልሳን ፈጣን የተባባሪ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያገኘች፣ የመጀመርያዋ ሴት የአካዳሚ ጉዳዮች ተባባሪ ምክትል ፕሬዚዳንት፣ ከዚያም የውጭ ግንኙነቶችና ትብብር ክፍል የመጀመርያዋ ሴት ምክትል ፕሬዚዳንት፣ ከ20 በላይ ጥናታዊ ፅሁፎች የታተሙላት፣ በስነምህዳር ጥበቃ የምትሳተፍ ወቅታዊ ሁኔታ የትውልድ ቦታ: ደብረማርቆስ፣ ጎጃም፣ ኢትዮጵያ የትውልድ ዘመን: 1968 ወቅታዊ መኖሪያ ስፍራ አዲስ አበባ፣ የመጀመሪያ […]