የመረጃ ጥንቅሩና እና የ”ፈልጊ” አገልግሎቱ አጠቃቀም

የመረጃ ጥንቅር፤– በተጠናቀረው መረጃ ውስጥ የተካተቱትን ሴቶች በዝርዝር ማየት ትችላላችሁ። መረጃዎቹ፣ በስም፣ በዋና የስራ ዘርፍ፣ በትውልድ ዘመን፣ በትውልድ ቦታ፣ በወቅታዊ የመኖርያ ስፍራ፣ እንዲሁም በባለታሪክ ዘመን (ታሪካዊ ወይም የዘመናችን) በሚል ተደራጅተው ቀርበዋል።

የ”ፈልጊ” አገልግሎት፡  በዋናው የድረገፁ መግቢያ (ቤታችን) ላይ ባለው የመፈለጊያ ሳጥን ውስጥ፣ ስም ወይም ጠቋሚ ቃል (ለምሳሌ፣ ሳይንቲስት፣ ፓይለት፣ ባህርዳር… ወይ ሌላ ጠቃሚ ቃል) በመፃፍ የባለታሪክ ሴት መረጃ ማፈላለግ ትችላላችሁ። የፃፋችሁትን ስም ወይም ጠቋሚ ቃል፣ በበርካታ ሴቶች ታሪክ ውስጥ የተጠቀሰ ከሆነ፤ የባለታሪኮቹን ሴቶች ስም ዝርዝር ይደረድርላችኋል – የ’ፈልጊ” አገልግሎቱ።

ማሳሰቢያ፡  የዘመኑ ሴቶች ታሪክ ውስጥ የተካተተው መረጃ በሙሉ ከራሳቸው ከሴቶቹ ጋር በተካሄደ ቃለምልልስ የተገኘና ባለታሪኮቹ ይሁንታቸውን የሰጡበት ነው። መረጃዎቹን በሌላ መንገድ ለማረጋገጥ የተደረገ ሙከራ የለም።

Posted on October 2, 2014 By admin