አቤጊያ ጌታቸው ፡- በ1983 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የተወለደችው አቤጊያ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት የአምስተኛ አመት ተማሪ ስትሆን፣ በ2006 ዓ.ም በኤል ኤል ቢ ዲግሪ እንደምትመረቅ ይጠበቃል፡፡ በህግ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚካሄደው ‘ቢጫ ንቅናቄ’ (በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት የማጥፋት ዘመቻ) አባል ስትሆን፣ በ1995 ዓ.ም በተካሄደው የጆን ሲ ማርሻል ሙት ኮርት የተሰኘ የችሎት ውድድር ላይ፣ በቺጋጎ ኢሊኖይስ የሚገኘውን የሴቶች ቡድን በመወከል ተሳትፋለች፡፡

 

አስተዋይ በቀለ ፡- በ1984 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የተወለደችው አስተዋይ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት የአራተኛ አመት ተማሪ ስትሆን፣ በ2007 ዓ.ም በኤል ኤል ቢ ዲግሪ እንደምትመረቅ ይጠበቃል፡፡ በህግ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚካሄደው ‘ቢጫ ንቅናቄ’ (በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት የማጥፋት ዘመቻ) አባል ናት፡፡

 

ቤቴል በቀለ ብርሃኑ፡- በኦሮሚያ ክልል በመተሃራ ከተማ በ1981 ዓ.ም የተወለደችው ቤቴል፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአለማቀፍ ግንኙነት መስክ ስትከታተለው የነበረውን የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት በከፍተኛ ውጤት በማጠናቀቅ በ2005 ዓ.ም ተመርቃለች፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካል ሳይንስና አለማቀፍ ግንኙነት በ2003 ዓ.ም ተቀብላለች፡፡  በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ  በመምህርነት ካገለገለች በኋላ በአሁኑ ሰዓት በስዊዘርላንድ የዶክትሬት ድግሪ ትምህርቷን እየተከታተለች ትገኛለች፡፡

 

ቢታንያ ጥላዬ ፡-በ1979 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የተወለደችው ቢታኒያ፣ የመጀመሪያ ዲግሪዋን በህግ እንዲሁም ሶሺዮሎጂና ሶሻል አንትሮፖሎጂ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2004 ተቀብላለች፡፡ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለሁለተኛ ዲግሪዋ የሰላምና ደህንነት ጥናቶች እየተከታተለች ሲሆን የሁለተኛ አመት ተማሪ ናት፡፡

 

ሃና አርአያስላሴ ፡-በ1981 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የተወለደችው ሃና፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት ፐብሊክ ስትሪም በተባለ ልዩ ዘርፍ በ2005 ከተመረቀች በኋላ የሎው ሪቪው ረዳት አዘጋጅ በመሆን ሰርታለች፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው የፍትህና ህጋዊ ስርዓት ጥናት ተቋም ውስጥ ጥናቷን ካካሄደች  በኋላ በአሁኑ ወቅት በማኪንሴይ ኤንድ ካምፓኒ በአማካሪነት  በመስራት ላይ ትገኛለች፡፡

 

ሃወይኒ ሃብቴ ፡- በ1980 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የተወለደችው ሃወይኒ፣ ከሃረማያ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት በ2004 ዓ.ም በኤል ኤል ቢ ዲግሪ ተመርቃለች፡፡ አዲስ አበባ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት ውስጥ በረዳት ፕሮግራም ኦፊሰርነት ስታገለግል የቆየችው ሃወይኒ፣  በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ አየር መንገድ በሥልጠና ላይ ትገኛለች፡፡

 

ሄለን ተስፋዬ ፡- በ1982 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የተወለደችው ሄለን፣ ከሃረማያ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት በ2004 ዓ.ም በኤል ኤል ቢ ዲግሪ ተመርቃለች፡፡ ለሰባት ወራት ያህል በኢትዮጵያ የሴቶች ማህበራት ቅንጅት በበጎ ፈቃደኝነት ካገለገለች በኋላም፣ በአሁኑ ወቅት በኢፌዲሪ ፍትህ ሚኒስቴር በአቃቢ ህግነት በመስራት ላይ ትገኛለች፡፡

 

ህይወት ደስታ ፡- በ1978 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ የተወለደችው ህይወት፣ የሬዲዮና የህትመት ጋዜጠኛ ስትሆን፣ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ የሴቶች ማህበራት ቅንጅት የኮሚኒኬሽን ኦፊሰር ሆና በመስራት ላይ ትገኛለች፡፡ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ በህግ የመጀመሪያ ዲግሪ ተቀብላለች፡፡

 

ሊዲያ አቶምሳ ቱጁባ ፡- በ1973 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የተወለደችው ሊዲያ፣ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት በ1997 ዓ.ም በኤል ኤል ቢ ዲግሪ ተመርቃለች፡፡ ኖርዌይ ከሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ኦስሎው በ2000 ዓ.ም በህግ የሁለተኛ ዲግሪዋን ተቀብላለች፡፡ በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ በሚገኘው የደህንነት ጥናቶች ኢንስቲቲዩት በመስራት ላይ የምትገኘው ሊዲያ የሁለት ልጆች እናት ናት፡፡ የዚህ ፕሮጀክት ዋና አስተባባሪም ናት፡፡

 

ማሪያማዊት እንግዳወርቅ ካሳ፡- በ1982 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የተወለደችው ማሪያማዊት፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2004 ዓ.ም በህግ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ተቀብላለች፡፡ በታደሰ ኪሮስ የህግ ቢሮና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ቢሮ በተመራማሪነት ልምምድ ካደረገች በኋላ፣ በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ በሚገኘው የደህንነት ጥናቶች ኢንስቲቲዩት በተለማማጅነት በመስራት ላይ ትገኛለች፡፡

 

ማህሌት ተስፋዬ ዘውዴ ፡- በ1981 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የተወለደችው ማህሌት፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2003 ዓ.ም በፍልስፍና የመጀመሪያ ዲግሪዋን ተቀብላለች፡፡ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በረዳት ምሩቅነት፣ በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት አገልግላለች፡፡ በአሁኑ ሰዓት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እየሰራች ሲሆን ተለማማጅ ዲፕሎማትም ናት፡፡

 

ማክዳ ሽመልስ ፡- በ1985 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የተወለደችው ማክዳ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት የአራተኛ አመት ትምህርቷን በመከታተል ላይ ስትሆን በ2007 ዓ.ም ትመረቃለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በህግ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚካሄደው ‘ቢጫ ንቅናቄ’ የተሰኘ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት የማጥፋት ዘመቻ አባል ናት፡፡

 

 

ሜላት ተክለጻድቅ ፡-  በ1971 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የተወለደችው ሜላት፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ1995 ዓ.ም በአካውንቲንግ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ተቀብላለች፡፡ በአሁኑ ወቅት በኢንድራ ጋንዲ ዩኒቨርሲቲ በሶሺዎሎጂ የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርቷን በርቀት ለመከታተል በዕጩ ተወዳዳሪነት ቀርባለች፡፡ በአለማቀፍ ትምህርት ኢንስቲቲዩት የአፍሪካ የልህቀት ማዕከል ፕሮጀክት ፕሮግራም ዳይሬክተር ናት፡፡ ለሰባት አመታት ያህል የወጣት ሴቶች ክርስቲያናዊ ማህበር( YWCA) የኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር በመሆን አገልግላለች፡፡ ሜላት በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ የድህረ ምረቃ ትምህርቷን እየተከታተለች ትገኛለች፡፡

 

ምንትዋብ አፈወርቅ ፡- በ1984 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የተወለደችው ምንትዋብ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት የአምስተኛ አመት ተማሪ ስትሆን፣ በተለይም ለአለማቀፍ ህግ ከፍተኛ ፍላጎት አላት፡፡ በህግ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚካሄደው ‘ቢጫ ንቅናቄ’ የተሰኘ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት የማጥፋት ዘመቻ አባል ስትሆን፣ በ2005 ዓ.ም ሽንግተን ዲሲ ውስጥ በተካሄደው ጄሳፕ ኢንተርናሽናል ሙት ኮርት የተሰኘ የችሎት ውድድር ላይ፣ የመጀመሪያውን የኢትዮጵያ የሁሉም ሴቶች ቡድን አባል በመሆን ተሳትፋለች፡፡ ምንትዋብ  አብረዋት ከሚማሩ ተማሪዎች የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ነው የተመረቀችው፡፡

 

ረድኤት እስጢፋኖስ ፡- በ1983 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የተወለደችው ረድኤት፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህግ ት/ቤት የአምስተኛ ዓመት ተማሪ ስትሆን በህግ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚካሄደው ‘ቢጫ ንቅናቄ’ (በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት የማጥፋት ዘመቻ) አባል ናት፡፡ የክፍሏ ፕሬዚዳንት ስትሆን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሴቶች በተዘጋጀው የወጣት ሴቶች አጋርነት ላይ ተሳትፋለች፡፡

 

ሬኔ ሁፍማን ፡- በ1973 ዓ.ም በአሜሪካ ወተርሉ፣ አዮዋ ግዛት የተወለደችው ሬኔ ሁፍማን፣ከሆዋርድ ዩኒቨርስቲ በሶሻል ዎርክ የማስተርስ ድግሪዋን ይዛለች፡፡ በሰዎች ዝውውርና በአስገዳጅ የጉልበት ሥራ ዙሪያ ልምድ ያላት ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት ውስጥ አማካሪ ናት፡፡

 

ሰምሐል ኪሮስ ፡- በ1981 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የተወለደችው ሰምሐል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በ2003 ዓም በሳይኮሎጂ የመጀመርያ ድግሪዋን አግኝታለች፡፡ በበጎፈቃደኝነት ከሰራች በኋላ በኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት ውስጥ ከሁለት ዓመት በላይ ያገለገለች ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በ THEO ኢንተርናሽናል ጄነራል ትሬዲንግ ኤልኤልሲ በዱባይ ቢሮዋቸው በሶርሲንግ ኤንድ ፎርዋርዲንግ ስፔሻሊስትነት በመስራት ላይ ትገኛለች፡፡

 

ሸዊት ወልደሚካኤል ፡-  በ1977 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የተወለደችው ሸዊት፣ ከዩኒቲ ዩኒቨርስቲ በማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተም ቢኤ ድግሪዋን የተቀበለች ሲሆን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሶስዮሎጂና በሶሻል አንትሮፖሎጂ ቢኤ ድግሪ ይዛለች፡፡ አሁን በሴንተር ፎር ዴቬሎፕመንት ኮንሰልቲንግ በፕሮግራም ኦፊሰርነት እየሰራች ጎን ለጎን ለማስተርስ ድግሪዋ የሰላምና ደህንነት ጥናቶች ትምህርቷን ትከታተላለች፡፡

 

ትዝታ ታደሰ ተክለፃዲቅ ፡- በ1978 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የተወለደችው ትዝታ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በስርዓተ ፆታ ጥናቶች የማስተርስ ድግሪዋን የተቀበለች ሲሆን ከህግ ፋከልቲ ደግሞ LLB ይይዛለች፡፡ ሰስቴይኔብል ኢንቫየሮንመንት ኤንድ  ዴቨሎፕመንት አክሽን (SEDA) ውስጥ በሥርዓተ- ፆታና ማህበራዊ ልማት ፕሮግራም  አስተባባሪነት ለሁለት ዓመት ከሰራች በኋላ በአሁኑ ሰዓት በቻይልድ ፈንድ ውስጥ በሕፃን ጥበቃና በሥርዓተ ፆታ ፕሮግራም ኦፊሰርነት እያገለገለች ትገኛለች፡፡  ትዝታ “Violence Beyond Control in the 21st Century: The Case of Ethiopian Domestic Workers in Middle East Countries”በሚል ርዕስ መፅሐፍ አሳትማለች፡፡

 

ወደርየለሽ አበበ፡- በ1982 ዓ.ም በአማራ ክልል በጎንደር የተወለደችው ወደርየለሽ፣ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ዲፕሎማሲና ዓለምአቀፍ ግንኙነት እያጠናች ነው፡፡ በ2003 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በፖለቲካል ሳይንስና በዓለም አቀፍ ግንኙነት የባችለር ድግሪዋን አግኝታለች፡፡ በአሁኑ ሰዓት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተለማማጅ ዲፕሎማት ናት፡፡

Posted on October 7, 2014 By admin With 0 comments

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Required fields are marked *
Your email address will not be published.

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>