“የኢትዮጵያ ሴቶች ትንሳኤ”፣ እጩ እንዲጠቁሙ ይጋብዝዎታል

መካተት አለባት ብለው የሚያስቧት ኢትዮጵያዊ ስኬታማ ሴት የሚያውቁ ከሆነ፤ ስሟንና አድራሻዋን፣ እንዲሁም ለምን በእጩነት እንደመረጧት የሚጠቁም ጥቂት መረጃ በኢሜይል ይላኩልን። በእጩነት የመረጧት ሴት፣ ቀድሞ በታሪክ የነበረች ወይም የአሁን ዘመን ልትሆን ትችላለች።  የአድራሻ ገፅ የሚለውንም በመጠቀም መልእክታችሁን ልታደርሱን ትችላላችሁ።

እጩ ለመምረጥ ስታስቡ፣ ግምት ውስጥ ልታስገቧቸው የሚገቡ ነጥቦች፡

*የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነች (በኢትዮጵያ የምትኖርም ሆነ ዳያስፖራ)፤ ወይም የውጭ ዜጋ ብትሆንም ኢትዮጵያ ውስጥ ጉልህ ስራ ያከናወነች፤

* በተሰማራችበት የሥራ መስክ ስኬት የተቀዳጀች፣ ህብረተሰቡ ስለ ሴቶች ካለው የዘልማድ አመለካከት ጋር ታግላ፣ ለሴቶች ታጥሮ ከተከለለው ልማዳዊ ሚና ባሻገር ተጉዛ ህልሟን እውን ያደረገች፤

*አንድም የሴቶችን ግስጋሴ የሚገድቡ መሰናክሎችን ሰባብራ፣ አልያም በራሷ ህይወትም ሆነ በማህበረሰብ ውስጥ ያሉ እንቅፋቶችን በመጋፈጥ አሸንፋ፣ ወይም በተሰማራችበት እመርታ አስመዝግባ ስኬትን የተቀዳጀት፤

*ዝነኛ ብትሆንም ባትሆንም፣ በስኬቷ ገና በሰፊው ብትታወቅም ባትታወቅም፤ በአካባቢዋ ወይም በኢትዮጵያ አሊያም በዓለም ደረጃ ትርጉም ያለው ለውጥ ለመፍጠር የቻለች፤

በፈተናዎች የማይበገር ቁርጠኝነትንና ድፍረትን፣ አልሸነፍ ባይነትንና ፅናትን በማሳየት፤ የወጣት ሴቶችን መንፈስ ለማነቃቃት የሚችሉ የሕይወት ታሪኮች፣ ይበልጥ ተፈላጊ ናቸው። በተጨማሪም፣ ሌሎች ሰዎችን ለመርዳት ትጋት የሚያሳዩ ሴቶችም ታሪካቸው በጣም ይፈለጋል። የሚመርጧት እጩ በማንኛውም የእድሜ ክልል ላይ የምትገኝ፤ በህይወት ያለች ወይም በህይወት የሌለች ልትሆን ትችላለች።

መረጃዎቻችንን ለማሻሻል ያግዙን !

በዚህ ድረገፅ የቀረቡ ባለታሪክ ሴቶችን በሚመለከት፣ ታሪኩን የሚያበለፅግ ተጨማሪ መረጃ የሚያውቁ ከሆነ፣ ወይም የተዛባ ታሪክ ለማረም የሚረዳ መረጃ ካለዎት፤ እባክዎ የአድራሻ ገፅ የሚለውን በመጠቀም በኢሜይል ይላኩልን። ይሄም በማድረግ ታሪኮቹ ይበልጥ ትክክለኛና ጠቃሚ እንዲሆኑ ያግዙን።

ለተሳትፎዎ እጅግ በጣም እናመሰግናለን

Posted on October 2, 2014 By admin